ኢንስቲትዩቱ በሲቪል ሰርቪስ ማኑዋሎችና መመሪያዎች ላይ ለመላ ሠራተኞቹ ሥልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለመላው ሰራተኞቹ በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር  በተዘጋጁ የስልጠና ሰነዶችና ማንዋሎች ላይ ሥልጠና ሰጠ፡፡

ከህዳር 18/2010 ጀምሮ ለ7 ቀናት 1. ውጤት ተኮር ስልጠናን ሥርዓት፣ 2. የመንግስት ሰራተኞች የስነ-ምግባር ኮድ፣ 3. የዜጎች ቻርተር፣ 4. የመልካም አስተዳደር፣ 5. የስብሰባ ስርዓት /መመሪያ/፣ 6. የለውጥ መሳሪያዎች ትስስር፣ እና 7. የሕዝብና የመንግስት ክንፍ ትስስር በሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና ሰጠ፡፡ በሥልጠናው ሁሉም ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን በያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳዮች ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ እንደተናገሩትም ሥልጠናው መልካም አስተዳደርንና ተቋማዊ ለውጥን አስመልክቶ በየጊዜው የሚሰጡ እንደዚህ ዓይነት ሥልጠናዎች አመለካከትን ለመቀየርና ጠንካራ ሲቪል ሰርቪስ ለመፍጠር ክፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዘነበ ጋረደው በሥልተናው ማጠናቀቂያ ለይ እንደተናገሩት የአመለካከት ችግር በስልጠና ብቻ አይቀረፍም፤በ1ለ5 ውይይቶችና በተለያዩ መድረኮች ለመለወጥ ባለን ተነሳሽነት ልክ ከተንቀሳቀስን የአመለካከት ለውጥ የማይመጣበት ምክንያት አይኖርም፡፡ ‘የሰው ጭንቅላት ያልተገለፀ መፅሀፍ ነው!’ የሚባለው ለዚህ ነው ያሉ ሲሆን፤ ሥልተና የተሰጠባቸው መመሪያዎች ተደራጅተው ከሲቪል ሰርቪስ እስከሚላኩ ድረስ፤ ራሳችንን ዝግጁ ማድረግ ይገባል! ሁላችንም የምንሰራው ለሀገራችን ነው፤ ከዚያ በመቀጠል ለራሳችን፤ ሀገር ተቀየረች ማለት እኛም በማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ደረጃችን ተቀየርን ማለት ነው! የሁላችን ርብርብ የተቋማችንና የሀገራችንን ስኬት እንደሚያፋጥን አውቀን ጠንክረን መሥራት ይጠበቅብናል በማለት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡