የኢንሰቲትዩቱ ሰራተኞች 12ኛውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፤ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከበሩ

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች 12ኛውን የኢትዮጵያ ብሄሮች፤ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በተቋም ደረጃ አከበሩ፡፡ በዓሉ‘’ በሕገ-መንግስታችን የደመቀ ሕብረ-ብሄራዊነታችን ለህዳሴያችን!’’ በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን የመወያያ ፅሁፉ በአቶ ዋሲሁን ዓለማየሁ የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ቀርቧል፡፡

የተዘጋጀው የመወያያ ሰነድ ዋነኛ ትኩረቶች፡

የፌዴራል ስርዓት

  • የፌዴራሊዝም ታሪካዊ አመጣጥና መነሻ
  • የፌዴራሊዝም ስርዓትን መከተል ያለው ፋይዳ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ አንፃር
  • የፌዴራል ስርዓቶች የሚጋሩዋቸው መሰረታዊ ባህርያት
  • በእኛ ሀገር ነባራዊ ሁኔታ ልማትና ዴሞክራሲ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ መሆናቸው
  • በህብረ-ብሄራዊ የፌዴራል  ስርዓት መVላት የሚገባቸው
  • ዴሞክራሲ ፣
  • ሕገመንግስታዊነት፣
  • የመድብለ -ፓርቲ  ስርዓት  መኖር፣
  • በመፈቃቀድ ላይ  የተመሰረተ  የህዝቦች  ህብረት መኖር፣
  • የሰብአዊ መብቶች  ጥበቃ ፣
  • የአናሳ ቡድኖች  (Minorities)  ድምፅ  መሰማት፣
  • አብሮነትና ብዙህነትን  ማቀፍ፣
  • የመንግስታት ግንኙነት መኖር …. ወዘተ

በሀገር ደረጃ የፌዴራል ስርዓቱ ያስገኛቸው ስኬቶች

  • የሰብአዊና የዲሞክራሲያዊ  መብት  ጥያቄዎችን  የመለሰ ስርዓት መሆኑ፣
  • አንድነት ያስቀጠለ  ስርዓት መሆኑ፣
  • የመድብለ ፓርቲን ስርዓትን  ዕውን  ያደረገ  ስርዓት  መሆኑ፣
  • ከ10 ዓመታት በላይ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማስመዝገብ የቻለ ስርዓት መሆኑ፣
  • የማህበራዊና መሰረተ ልማት  አውታሮች  ልማት  እያረጋገጠ  የሚገኝ  ስርዓት መሆኑ፣
  • በአጠቃላይ በማህበራዊ፤ኢኮኖሚዊና ፖለቲካዊ መስኮች ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑ፡፡

የፌዴራል ስርዓቱ ላይ እያጠሉ ያሉ እሳቤዎችና ተግባራት

  • በሕገ-መንግስታችን ዙሪያ የጋራ አረዳድና ግንዛቤ በሚፈለገው ደረጃ አለመኖር፤
  • የትምክህትና ጠባብ አስተሳሰብ የወለዳቸው ችግሮች አሁንም ያልተፈቱ መሆን፤
  • የሃይማኖት አክራሪነት
  • የኪራይሰብሳቢነት አዝማሚዎችና ተግባራት
  • የኮንትሮባንዲስቶች እንቅስቃሴ መኖር
  • ከአስተዳደር ወሰንና መሰል ጉዳዮች ጋር ተያይዞ አልፎ አልፎ ግጭቶች መከሰታቸው

ቀጣይ አቅጣጫዎች

1)  የመከባበር ፣ መደማመጥ፣ መቻቻል፣ መደጋገፍ፣ መተባበር ባህልን ማጎልበት ፣ብዙህነትን ማክበር፣

2)  የጋራ ማንነት መገለጫዎችን ማጎልበት፣

3)  የመንግስታትና የህዝቦች ግንኙነቶችን ማጠናከር፣

4)  ሕገ-መንግስትና ሌሎች የስርዓቱ ሕጎችን ማክበርና መጠበቅ፣

5)  ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ መላ ሃብትን ማነቀሳቀስና መረባረብ፣

6)  ጎጂ የውጭ ፖለቲካን (Imported Politics) ማስወገድ፣

በቀረበው ሰነድ መነሻነት ከወቅታዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፤በተለይም ከፌዴራል ስርዓቱ ጋር ተያይዞ በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ ሰራተኞች ጥያቄዎችና አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን፤ ውይይቱን የመሩት አቶ ዋሲሁን ዓለማየሁ  እና ወ/ሮ ገንዘቤ ተስፋዬ የኢንስቲትዩቱ የሰው ሀብት ስራ አመራር ዳይሬክተር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡  በመጨረሻም የፌዴራላዊ ስርዓቱን አደጋዎች ጠንቅቆ በማወቅ በየጊዜው መልካቸውን እየቀየሩ የሚመጡ ችግሮችን የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች በጋራ መታገል እንደሚገባቸው መግባባት ላይ በመድረስ የበዓሉ ፍፃሜ ሆኗል፡፡

ኢንስቲትዩቱ በሲቪል ሰርቪስ ማኑዋሎችና መመሪያዎች ላይ ለመላ ሠራተኞቹ ሥልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለመላው ሰራተኞቹ በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር  በተዘጋጁ የስልጠና ሰነዶችና ማንዋሎች ላይ ሥልጠና ሰጠ፡፡

ከህዳር 18/2010 ጀምሮ ለ7 ቀናት 1. ውጤት ተኮር ስልጠናን ሥርዓት፣ 2. የመንግስት ሰራተኞች የስነ-ምግባር ኮድ፣ 3. የዜጎች ቻርተር፣ 4. የመልካም አስተዳደር፣ 5. የስብሰባ ስርዓት /መመሪያ/፣ 6. የለውጥ መሳሪያዎች ትስስር፣ እና 7. የሕዝብና የመንግስት ክንፍ ትስስር በሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና ሰጠ፡፡ በሥልጠናው ሁሉም ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን በያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳዮች ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡ ተሳታፊዎቹ እንደተናገሩትም ሥልጠናው መልካም አስተዳደርንና ተቋማዊ ለውጥን አስመልክቶ በየጊዜው የሚሰጡ እንደዚህ ዓይነት ሥልጠናዎች አመለካከትን ለመቀየርና ጠንካራ ሲቪል ሰርቪስ ለመፍጠር ክፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዘነበ ጋረደው በሥልተናው ማጠናቀቂያ ለይ እንደተናገሩት የአመለካከት ችግር በስልጠና ብቻ አይቀረፍም፤በ1ለ5 ውይይቶችና በተለያዩ መድረኮች ለመለወጥ ባለን ተነሳሽነት ልክ ከተንቀሳቀስን የአመለካከት ለውጥ የማይመጣበት ምክንያት አይኖርም፡፡ ‘የሰው ጭንቅላት ያልተገለፀ መፅሀፍ ነው!’ የሚባለው ለዚህ ነው ያሉ ሲሆን፤ ሥልተና የተሰጠባቸው መመሪያዎች ተደራጅተው ከሲቪል ሰርቪስ እስከሚላኩ ድረስ፤ ራሳችንን ዝግጁ ማድረግ ይገባል! ሁላችንም የምንሰራው ለሀገራችን ነው፤ ከዚያ በመቀጠል ለራሳችን፤ ሀገር ተቀየረች ማለት እኛም በማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ደረጃችን ተቀየርን ማለት ነው! የሁላችን ርብርብ የተቋማችንና የሀገራችንን ስኬት እንደሚያፋጥን አውቀን ጠንክረን መሥራት ይጠበቅብናል በማለት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

The Second Joint Coordination Committee (JCC) meeting held in EWTI

Ethiopian Water Technology Institute (EWTI) and Japan International cooperation Agency (JICA) Joint coordination committee (JCC) have discussed about various issues which strengthen the bilateral relation focus on Technical and material supports. The discussion was targeting evaluating both sides undertaking activities which strengthen the trainings given by EWTI.  Different issues regarding the performances of EWTI and JICA were raised.

The discussion issues include:-

  • The Baseline Survey Of The Status Of EWTI
  • Technical Gap Finding Survey Conducted By JICA
  • Results Of The Joint Monitoring Results
  • Promotional activities produced in coordination (newsletters, table calendar, etc)

All the above and related issues were discussed by the members in details.

According to reports during the Joint coordination committee meeting, the following achievements (outputs) are gained by JICA’s activates after the first JCC meeting:-

  1. Training management structure of EWTI is strengthened through PDCA cycle;
  2. Training capacity of EWTI’s trainers is enhanced through pilot training courses;
  3. Implementation structure of Internal Training for EWTI’s trainers is established;

Finally, the committee has highlighted the next steps to be done in modernizing the training delivered by EWT to water sector.

የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ከተፈናቀሉት ወገኖቻችን ጎን እንደሚቆሙ አረጋገጡ

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት ሠራተኞች በዛሬው ዕለት ባደረጉት ውይይት በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በተከሰተው ግጭት ከተፈናቀሉት ወገኖቻችን ጎን እንደሚቆሙ አረጋገጡ፡፡

ውይይቱን የመሩት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዘነበ ጋረደው እንደገለጹት ‘’በአሁኑ ጊዜ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በተለየዩ ጊዜያት በነበሩት ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ወገኖቻችንን ሲረዱ የነበሩ ሲሆን፤ አሁን በተፈጠረው ችግር እነሱ ተረጂ ሆነው የእኛን አለሁ ባይነት ይሻሉ፡፡ በዚህ አደጋ ተጎጂ የሆኑት እናቶችና ህጻናት እንዲሁም አረጋውያን መሆናቸው ችግሩን የከፋ ያደርገዋል፤ በየዕለቱ በተጠለሉበት ካምፕ እየወለዱ ያሉ እናቶች በርካቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ እንደ ዜግነታችንና ሰብአዊነታችን ከነዚህ ወገኖች ጎን መቆም አለብን ብለዋል!’’

በመድረኩ ሀሳባቸውን የሰጡ ሰራተኞችም የችግሩን ስፋት እና አሳሳቢነት በየጊዜው እየሰሙ መሆናቸውን ገልጸው እነዚህን ወገኖቻችንን ለመርዳት እስካሁን ድረስም መዘግየት አልነበረብንም ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ይህ ጉዳይ የሁላችንም ግዴታ በመሆኑ ለወገኖቻችን አለኝታ መሆናችንን መግለጽ አለብን ሲሉ አጋርነታቸውን ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ሁሉም የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች የግማሽ ወር ደመወዛቸውን ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ለመርዳት ቃል ገብተዋል፡፡

ለቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጆች በሚደረገው ድጋፍ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የውሃ ዘርፉን አቅም ግንባታ ለመደገፍ ከሚሰራቸው ሥራዎች መካከል በውሃ ላይ የሚያሰለጥኑ ተቋማትን የሰው ኃይልና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ድጋፍ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ባለፈው ዓመት በርካታ ሥራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

በዛሬው ውይይትም ባለፈው ዓመት የተከናወኑ አንኳር ተግባራትና በ2010 በጀት ዓመት ሊከናወኑ የተቀዱ ተግባራት በአቶ ዓለማየሁ ጉደታ የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ድጋፍ ፕሮግራምና ምዘና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቀርቧል፡፡ አቶ ዓለማየሁ እንደ ተናገሩት የውሃ ዘርፉን የሰው ኃይል አቅም ግንባታ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የቴ/ሙ/ት/ሥልጠና ኮሌጆችን ሁለንተናዊ አቅም ማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ ሥራ ነው፤ ይህንን ከግብ ለማድረስም የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ አለባቸው፡፡

የ2010 ዕቅድ ከቀረበ በኋላ በክቡር ዋና  ዳይሬክተሩ አቶ ዘነበ ጋረደው አወያይነት ተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡ ክቡር አቶ ዘነበ ውይይቱን ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት ከየኮለጆቹና ከሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ተሳታፊዎች የሚሰጠን ግብአቶች ዕቅዱን አደብረን ወደ ሥራ ለመግባት ያስችለናል፡፡

ከየኮሌጆቹ የተገኙ እና ከፌዴራል ቴ/ሙ/ት/ሥልጠና ኤጀንሲ የተገኙ ተሳታፊዎችም በቀረበው ዕቅድ ላይ ሀሳቦቻቸውን ሰጥተዋል፡፡ እነሱ እንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ ለቅም ግንባታ እየሰራ ያለው ሥራ ውጤታማ ነው፤ ከዚህ የላቀ ሥራ ለመሥራትም ከሚመለከታቸው ተባባሪ አካላት ጋራ በመሆን መንቀሳቀስ ይጠበቃል፡፡

ኢንስቲትቱ የተከለሱ የዘርፉ የሙያ ደረጃዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በቢሾፍቱ እያካሄደ ነው

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በውሃው ዘርፍ የልህቀት ማዕከል በመሆን የዘርፉን አቅም ግንባታ በሳይንሳዊ መንገድ ለመምራት ራዕዩን ለማሳካት በርካታ እየሰራ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ሥራዎች መካከልም 5 የሙያ ደረጃ ክለሳ፤ የሞዴል ካሪኩለም ቀረጻ እና የብቃት ምዘና መሳሪያዎች ዝግጅት ባለፈው በጀት ዓመት አጠናቋል፡፡ እነዚህ የሙያ ደረጃዎች በዘርፉ ዓለም የደረሰችበት ደረጃ ለመድረስ እንዲቻል የሌሎች ሀገራት ምርጥ ተሞክሮዎች ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር ተጣጥሞ እንዲካተትባቸው ተደርጓል፡፡ የሙያ ደረጃዎቹ ተገቢውን ግምገማ ከተደረገላቸው በኋላ በውሃ፤ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ፀድቀው ለትምህርት ሚኒስቴር ተልከዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴርም የቀረበለትን የሙያ ደረጃዎች ተገቢነት በማረጋገጥ በውሃ ዘርፍ ላይ ሥልጠና እየሰጡ ለሚገኙ ለ9ኙ የቴ/ሙ/ት/ስ/ ተቋማት መላኩን ልኳል፡፡ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ከኢንስቲትዩታችን ጋር በነበራቸው ግንኙነት ወቅት በተላከው ሰነድ ላይ አንዳንድ የግልጽነት ጥያቄዎችና ማብራሪዎች እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡

 

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ዘነበ ጋረደው በመክፈቻ ንግግራቸው የዘሬውን መርሐግብር ዓለማ ሲገልጹ እንደተናገሩት በነዚህ 5 የሙያ ደረጃዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው፡፡ ይህ የግንዛቤ መስጫ መድረክ በዘርፉ የሚሰጡ ሥልጠናዎች ጥራታቸውን እንዲጠብቁና ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት የላቀ ሚና ከመጫወቱም በላይ ሁሉም የዘርፉ ባለድርሻዎች ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የምናደርገውን ጥረት እንዲያግዙ ይረዳል፡፡

 

በመድረኩ ላይ ክብርት ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ ክቡር አቶ ተሾመ ለማ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ የውሃ፤መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ የፌዴራል ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኤጀንሲ ባለሙያዎች፣ የ9ኙ የቴ/ሙ/ት/ሥ/ተቋማት ሀላፊዎች እና የኢንስቲትዩታችን ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡

የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ተከበረ

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሰራተኞች 10ኛውን የሰንደቅ ዓለማ ቀን በድምቀት አከበሩ፡፡ ሥነ-ሥርዓቱን የመሩት የኢንሰቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘነበ ጋረደው ናቸው፡፡

ክቡር ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለጹት ሰንደቅ ዓለማ የህዝቦች አንድነት መገለጫ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለሰንደቅ ዓላማው ክብር ዘብ መቆም አለበት፡፡ ይህ የሚገለጸው ደግሞ በተሰማሩበት የሥራ መስክ ሁሉ ውጤታማ በመሆን የሀገር ክብር ከፍ በማድረግ ስለሆነ ዋነኛ ጠላታችን የሆነውን ድህነት በመወጋት ሀገራችንን ወደ ከፍታ ማማ ማሳደግ አለብን፡፡ “ራዕይ ሰንቀናል ለላቀ ድል ተነስተናል!” የሚለው የዘንድሮ መሪ ቃልም የከፍታ ዘመናችንን የሚልጽ በመሆኑ ይህንኑ መሪ ቃል ከግብ ለማድረስ መረባረብ እንዳለብንም አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡